ኦሪት ዘዳግም 19

1፤ አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን የሚሰጥህን አሕዛብ ባጠፋ ጊዜ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥

2፤ አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ በምድርህ መካከል ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ።

3፤ ነፍሰ ገዳይ ይሸሽባቸው ዘንድ ወደ እነርሱ የሚወስደውን መንገድ ታዘጋጃለህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የሚያወርስህን ምድር ከሦስት አድርገህ ትከፍላለህ።

4፤ የነፍሰ ገዳይ ወግ ይህ ነው፤ አስቀድሞ ጠላቱ ሳይሆን ባልንጀራውን ሳያስብ የገደለ ወደዚያ ሸሽቶ በሕይወት ይኑር።

5፤

6፤ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊቈርጥ ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉንም ሊቈርጥ ምሳሩን ሲያነሣ ብረቱ ከእጀታው ቢወልቅ፥ ባልንጀራውንም እስኪሞት ድረስ ቢመታው፥ ደም ተበቃዩ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናድዶ እንዳያሳድደው መንገዱም ሩቅ ስለ ሆነ አግኝቶ እንዳይገድለው፥ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖራል፤ አስቀድሞ ጠላቱ፤ አልነበረምና ሞት አይገባውም።

7፤ ስለዚህ እኔ። ለአንተ ሦስት ከተሞችን ለይ ብዬ አዝዤሃለሁ።

8፤ አምላክህም እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ዳርቻህን ቢያሰፋ፥ ይሰጣቸውም ዘንድ ለአባቶችህ የተናገረውን ምድር ሁሉ ቢሰጥህ፥

9፤

10፤ አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ ሁልጊዜም በመንገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ታደርጋት ዘንድ ብትጠብቅ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እንዳይፈስስ ደምም በአንተ ላይ እንዳይሆን፥ በእነዚህ በሦስት ከተሞች ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ።

11፤ ሰው ግን ባልንጀራውን ቢጠላ፥ ቢሸምቅበትም፥ ተነሥቶም እስኪሞት ድረስ ቢመታው፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥

12፤ የከተማው ሽማግሌዎች ይልካሉ፥ ከተማጠነበትም ከተማ ይነጥቁታል፥ እንዲሞትም በደም ተበቃዩ እጅ አሳልፈው ይሰጡታል።

13፤ ዓይንህ አትራራለት፤ ነገር ግን መልካም ይሆንልህ ዘንድ ንጹሑን ደም ከእስራኤል ታስወግዳለህ።

14፤ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር በምትወርሳት ርስትህ የቀደሙ ሰዎች የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።

15፤ ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማድረግም ስለ ሠራት ኃጢአት ሁሉ በማንም ላይ አንድ ምስክር አይቁም፤ በሁለት ምስክሮች ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ነገር ሁሉ ይጸናል።

16፤ በዓመፃ ይከስሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰተኛ ምስክር ቢቆም፥

17፤ ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤

18፤ ፈራጆቹም አጥብቀው ይመረምራሉ፤ ያም ምስክር ሐሰተኛ ምስክር ሆኖ በወንድሙ ላይ በሐሰት ተናግሮ ቢገኝ፥

19፤ በወንድሙ ላይ ያደርገው ዘንድ ያሰበውን በእርሱ ላይ ትመልሱበታላችሁ፤ እንዲሁም ከአንተ መካከል ክፋቱን ታስወግዳለህ።

20፤ የቀሩትም ሰምተው ይፈራሉ፥ እንደዚህ ያለውንም ክፋት ከመካከልህ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ አያደርጉም።

21፤ ዓይንህም አትራራለት፤ ነፍስ በነፍስ፥ ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ ይመለሳል።