መጽሐፈ ዕዝራ። 10

1፤ ዕዝራም እያለቀሰና በእግዚአብሔር ቤት ፊት እየወደቀ በጸለየና በተናዘዘ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ የወንድና የሴት የሕፃናትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።

2፤ ከኤላም ልጆች ወገን የነበረም የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው። አምላካችንን በድለናል፤ የምድርን አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፤ አሁን ግን ስለዚህ ነገር ገና ለእስራኤል ተስፋ አለ።

3፤ አሁንም እንደ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ እንደሚፈሩት ምክር፥ ሴቶችን ሁሉ ከእነርሱም የተወለዱትን እንሰድድ ዘንድ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ፤ እንደ ሕጉም ይደረግ።

4፤ ይህም ነገር ለአንተ ይገባልና፥ እኛም ከአንተ ጋር ነንና ተነሣ፥ አይዞህ፥ አድርገው።

5፤ ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹንና ካህናቱን ሌዋውያኑንም እስራኤልንም ሁሉ እንደዚህ ቃል ያደርጉ ዘንድ አማለ፤ እነርሱም ማሉ።

6፤ ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹም ኃጢአት ያለቅስ ነበርና ገብቶ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም።

7፤

8፤ ምርኮኞቹም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ፥ እንደ አለቆቹና እንደ ሽማግሌዎችም ምክር በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ሁሉ ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፥ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ እንዲለይ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አዋጅ ነገሩ።

9፤ ሦስት ቀንም ሳያልፍ በዘጠኝኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።

10፤ ካህኑም ዕዝራ ተነሥቶ። ተላልፋችኋል፤ የእስራኤልን በደል ታበዙ ዘንድ እንግዶችን ሴቶች አግብታችኋል።

11፤ አሁንም ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር ተናዘዙ፥ ደስ የሚያሰኘውንም አድርጉ፤ ከምድርም አሕዛብና ከእንግዶች ሴቶች ተለዩ አላቸው።

12፤ ጉባኤውም ሁሉ በታላቅ ድምፅ መልሰው እንዲህ አሉ። እንደ ተናገርኸን እናደርግ ዘንድ ይገባናል።

13፤ ነገር ግን የሕዝቡ ቍጥር ብዙ ነው፥ ጊዜውም የትልቅ ዝናብ ጊዜ ነው፥ በሜዳም ልንቆም አንችልም፤ በዚህም ነገር እጅግ በድለናልና ይህ ሥራ የአንድ ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም።

14፤ አለቆቻችንም በጉባኤው ሁሉ ፋንታ ይቁሙ፤ ስለዚህም ነገር የአምላካችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት በከተሞቻችን ያሉት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሁሉ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።

15፤ ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ሜሱላምና ሌዋዊውም ሳባታይ ረዱአቸው።

16፤ ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፥ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፤ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ።

17፤ እስከ መጀመሪያው ወር እስከ መጀመሪያው ቀን ድረስ ሠረተው እንግዶቹን ሴቶች ያገቡትን ሰዎች ሁሉ መርምረው ጨረሱ።

18፤ ከካህናቱም ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ፥ መዕሤያ፥ አልዓዛር፥ ያሪብ፥ ጎዶልያስ።

19፤ ሚስቶቻቸውን ይፈቱ ዘንድ እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም ከመንጋው አንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

20፤ ከኢሜር ልጆችም፤ አናኒና ዝባድያ።

21፤ ከካሪም ልጆችም መዕሤያ፥ ኤልያስ፥ ሸማያ፥ ይሒኤል፥ ዖዝያ።

22፤ ከፋስኩር ልጆችም፤ ኤልዮዔናይ፥ መዕሤያ፥ ይስማኤል፥ ናትናኤል፥ ዮዛባት፥ ኤልዓሣ።

23፤ ከሌዋውያንም፤ ዮዛባት፥ ሰሜኢ፥ ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፥ ፈታያ፥ ይሁዳ፥ አልዓዛር።

24፤ ከመዘምራንም፤ ኤልያሴብ፤ ከበረኞችም፤ ሰሎም፥ ጤሌም፥ ኡሪ።

25፤ ከእስራኤልም ከፋሮስ ልጆች፤ ራምያ፥ ይዝያ፥ መልክያ፥ ሚያሚን፥ አልዓዛር፥ መልክያ፥ በናያስ።

26፤ ከኤላም ልጆችም፤ ሙታንያ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ አብዲ፥ ይሬሞት፥ ኤልያ።

27፤ ከዛቱዕ ልጆችም፤ ዔሊዮዔናይ፥ ኢልያሴብ፥ ሙታንያ፥ ይሬሞት፥ ዛባድ፥ ዓዚዛ።

28፤ ከቤባይ ልጆችም፤ ይሆሐናን፥ ሐናንያ፥ ዘባይ፥ አጥላይ።

29፤ ከባኒ ልጆችም፤ ሜሱላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብ፥ ሸዓል፥ ራሞት።

30፤ ከፈሐት ሞዓብ ልጆችም፤ ዓድና፥ ክላል፥ በናያስ፥ መዕሤያ፥ ሙታንያ፥ ባስልኤል፥ ቢንዊ፥ ምናሴ።

31፤ ከካሪም ልጆችም፤ አልዓዛር፥ ይሺያ፥ መልክያ፥

32፤ ሸማያ፥ ስምዖን፥ ብንያም፥ መሉክ፥ ሰማራያ።

33፤ ከሐሱም ልጆችም፤ መትናይ፥ መተታ፥ ዛባድ፥ ኤሊፋላት፥ ይሬማይ፥ ምናሴ፥ ሰሜኢ።

34፤ ከባኒ ልጆችም፤ መዕዳይ፥ ዓምራም፥

35፤ ኡኤል፥ በናያስ፥ ቤድያ፥ ኬልቅያ

36፤

37፤ ወንያ፥ ሜሪሞት፥ ኤልያሴብ፥ መታንያ፥

38 መትናይ፥ የዕሡ፥ ባኒ፥ ቢንዊ፥ ሰሜኢ፥

39፤

40፤ ሰሌምያ፥ ናታን፥ ዓዳያ፥ መክነድባይ፥

41፤ ሴሴይ፥ ሸራይ፥ ኤዝርኤል፥ ሰሌምያ፥ ሰማራያ፥ ሰሎም፥ አማርያ፥ ዮሴፍ።

42፤

43፤ ከናባው ልጆችም፤ ይዔኤል፥ መቲትያ፥ ዛባድ፥ ዘቢና፥ ያዳይ፥ ኢዮኤል፥ በናያስ።

44፤ እነዚህ ሁሉ እንግዶቹን ሚስቶች አግብተው ነበር፤ ከእነዚህም ሚስቶች አያሌዎቹ ልጆችን ወልደው ነበር።